በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች፣ ለፍቅሩና ለቸርነቱ ወሰን የሌለው አምላካችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንኳን ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።
ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። ጥምቀት ከእግዚአብሔር የተሰጠን የዳግም መወለጃ ጸጋ ነው። ሰው በሥጋ ሲወለድ በሚታይና በሚዳሰስ ግዙፍ አካል ይወለዳል፤ በጥምቀት ሲወለድ ግን በማይታይ ድንቅና ረቂቅ በሆነ ምሥጢር ከመንፈስ ቅዱስ ይወለዳል። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ይህን የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ ቁልፍ የሆነውን ጥምቀታችንን ቀድሶ ይሰጠን ዘንድ በዮሐንስ እጅ ተጠምቆልናል። «ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ» እንዳለ ቅዱስ ያሬድ።
የጌታችንን በዓለ ጥምቀት የምናከብረው ዳግም ለመጠመቅ አይደለም፤ በዓሉን የምናከብረው ጌታችን የሰጠንን ታላቅ ጸጋ በማስታወስ ከበዓሉ ማግኘት የሚገባን ጸጋና በረከት ለማግኘት ነው። ተጨማሪ ያንብቡ
፩ኛ ዮሐ ፫፥፰
የዛሬ ሁለት ሺህ አራት ዓመት በምድራችን ድንቅ ነገር ተደረገ። እግዚአብሔር የሰው ልጅ በኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ በብዙ መንገድ በነቢያት አንደበት ሲያናግር የነበረውን ተስፋ ለመፈጸም ወደ ምድር መጣ። በንጽሐ ሥጋ በንጽሐ ነፍስ ፍጽምት ከሆነች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ ያለዘርዐ ብእሲ ተጸንሶ በፍጹም ድንግልና ተወለደ። በዚህም የማይወሰነው ተወሰነ፤ የማይታየው ታየ፤ የማይዳሰሰው ተዳሰሰ። የሰማይ መላእክትና እረኞች በሕልውና ከሰማይ አባቱ ሳይለይ ድንግል እናቱ የታቀፈችውን ጌታ አመሰገኑት። ሰብአ ሰገል ሰገዱለት እጅ መንሻም አቀረቡለት። ተጨማሪ ያንብቡ
ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤልየሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው። ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው።
ይህን ቃል የተናገረው ጠቢቡ ሰሎሞን ነው። ሰሎሞን ከመዝሙር የሚበልጥ መዝሙር ተብሎ በሚጠራው መጽሐፉ «ተመለሽ ተመለሽ» እያለ ደግሞ ደጋግሞ ይጣራል። ጥሪውን የሚያስተላልፈው ለእመቤታችን ነው። የኋላ የኋላ የሚሆነው ምሥጢር ተገልጦለት በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት መሰደዷን አይቶ «ስደቱ ይብቃሽ፣ አሁን ጊዜው ደርሷልና ወደ ሀገርሽ ናዝሬት ተመለሽ» ይላታል። በዚህ ቃል መሠረት እመቤታችን ለሦስት ዓመታት ያህል በስደት ከቆየች በኋላ ሄሮድስ መሞቱን መልአኩ ነግሯት ወደ ገዛ ሀገሯ ተመልሳለች። (ተጨማሪ ያንብቡ )
የሁለቱንም ቀን ጉባኤ በተመለከት የተዘጋጀውን ሪፖርት፣ ፎቶና ቪዲዮዎች ይህንን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ(ተጨማሪ ያንብቡ )
የምስራቅ ዞን የ2004 ዓ ም የመጀመርያ ዙር ጉባኤውን በዋሽንግተን ዲሲ አካሔደ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ የምስራቅ ዞን የ2004 ዓ ም የመጀመርያ ዙር ጉባኤውን መምህራነ ወንጌል፣ ዘማርያን፣ እንዲሁም ከየእስቴቱ የመጡ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በተገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ ግዛት ኖርዝ ዌስት ዲሲ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ከቀኑ ፯ ተኩል ከ፸ በላይ የሚሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት ዓባላት የተገኙበት መርሃግብር በጸሎት ተከፍቶ እንደተጀመረ የምስራቅ ዞን አጠቃላይ የስራ ሂደት እና አተገባበር {REPORT} በሂሳብ ክፍሉዋ ኃላፊአማካኝነት የቀረበ ሲሆን ከተሰብሳቢዎች የተነሱ ጥያቄዎችን በስራ አመራር ላይ ያሉ ወንድሞች መልሰዋል።
በእለቱ የተገኙት መምህር ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ ስለ አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ምንነት በሰፊው ካስተማሩ በኋላ ስለወቅታዊው የቤተክርስቲያን ፈተና በተለይም እንደሰደድ እሳት እየተፋፋመ ያለውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ እና ስለ ወቅታዊው የሰሜን አሜሪካ ቀኖና ቤተክርስቲያን መጣስ አስመልክቶ በሰፊው አወያይተዋል።
በትምህርቱ ብሎም በውይይቱ የወጣቶች ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት እንዲሁም ሁሉም ሰው ባለበት ጸንቶ በመቆም ስለ አንዲት ቤተክርስቲያን ጠበቃ እንዲቆም ግንዛቤ ማሳደር ተችሏል።ይህንንም ተከትሎ የስርአተ ቤተክርስቲያን መጣስ ያስቆጣቸው ወጣቶች ጥያቄያቸውን በግል ወይም በየሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች አሰምተዋል።
መርሃ ግብሩ የብዙዎችን ጥያቄ የመለሰና አበረታች እንደነበር በስፍራው የተገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናግረዋል:: በተጨማሪም ይህ አይነቱ መርሃግብር በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንዲደገም ከተለያዩ አካላት ጥያቄው ተደጋግሞ ቢነሳም የጉባኤው አዘጋጅ እንደ አሰራር ቀኑን ወስኖ መናገር ባይችልም እንኳን ከስራ አመራር አባላቱ ጋር ተገናኝቶ በቅርብ ጊዜ መርሃግብር እንደሚያዘጋጅ ቃል ገብቷል።
በመጨረሻም ከቀኑ፲፪ ተኩል የመርሃ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል። ከጉባኤው ዘግይቶ መጀመር ጋር ተያይዞ አንዳንድ መርሃ ግብሮች ቢታጠፉም ጉባኤው የታቀደለትን እቅድ ለማሳካት ችሏል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በገሊላ ቃና በዶኪማስ ቤት ድንግል አዛኝቱ የአምላክ እናት እድምተኛው በዝቶ ወይኑ ሲያልቅባቸው ጥብብ ጭንቅ ሲሉ ማጠፍያው አጥሯቸው ወይኑ በማለቁ ዳር ይደርሳል ያለው ተክዟል ዶኪማስ አለሁልህ በለው ልጄ ወይኑ አለቀ ብለሽ ስትነግሪው ጌታም በመታዘዝ ልዩ ወይን ሰጣቸው ብለሽ እንዳማለድሽ ከእፍረት እንዳዳንሽው ስለእኔም ባዶነት የኔ ጌታ በይው:: (ተጨማሪ ያንብቡ )