በሚኒሶታ ሚኒአፓሊስ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አስመረቀ
በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርትቤትበቀዳማይ/የመጀመሪያ/ እና በካዕላይ/ሁለተኛ/ ተከታታይ ትምህርት ያስተማራቸውን ፵፪ ተማሪዎች ቅዳሜ የካቲት ፲፱ ፳፻፫ ዓ.ም ካህናት አባቶች የቤተክርስቲያኒቱ አሰተዳዳር እና ምዕመናን በተገኙበት አስመርቋል፡፡ በምረቃውም ዕለት የነበረውን ሰፊ መርሐ ግብር አጠር ባለ መልኩ እንዲህ ነበር ፡ ለተጨማሪ መረጃ
ዐቢይ ጾም (የሁዳዴ ጾም)
ፈጣሪያችንና አምላካችን፥ጌታችንና መድሃኒታችን፥ካህን፡ ሊቀ ካህናታችንና ንጉሥ፡ ንጉሠ ነገሥታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ለእኛ፡ ለኹላችን ሲል፡ የፆመውን ፆምና የጸለየውን ጸሎት፥ያስተማረውን ትምህርትና ያደረጋቸውን ተአምራት፥የደረሰበትን ፈተናና የታገሣቸውን መከራዎች እያስታወስን፡ (ተጨማሪ ያንብቡ )

Skip Navigation Links
 የአንድነት ጉባኤው መተዳደሪያ ደንብ


 ከዴንቨር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የፈለገ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

የዴንቨር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተመሰረተው ሚያዝያ ፪ ቀን ፲፱፱፯ ዓ. ም ሲሆን፤ ለቤተክርስቲያኒቱ መመስረት ምክንያት የሆነውም በ ፲፱፺ ዎቹ በአብዛኛው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተፋፍሞ የነበረው የመለያት ችግር ሲሆን በዚሁ በዴንቨርም ቤተከርስቲያን የዘረኝነትና የፖለቲካ ዓላማ ማካሄጃ እንዳትሆን ይጋደሉ የነበሩ እውነተኛ ምዕመናን በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ነው፡፡ እነዚሁ ምዕመናን ከቤተክርስቲያኒቱ በፓሊስ ኃይል ተገደው እስኪወጡ ድረስ በመገፋታቸው በእምነታቸው በመጽናት ተጋድሎዋቸውን በመቀጠል በወቅቱ የአገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበረት በነበሩት በአቡነ ማትያስ መልካም ፈቃድና በእግዚአብሔር ቸርነት ቤተክርስቲያኒቱ ልትቋቋም ችላለች፡፡ ሰንበት ት/ቤቱም ይህንን ተከትሎ በግንቦት ፪ ቀን ፲፱፺፯ዓ ም ተቋቊሟል ፡፡ ሰንበት ት/ቤቱም በ ፳፻ ዓ. ም ፈለገ ህይወት የሚለውን መጠሪያ በአባቶች ተሰይሞለታል የፈለገ ህይወት ሰንበት ት/ ቤት በአሁኑ ወቅት ፴፭ የሚሆኑ አባላት አሉት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ )

የስቅለትና የትንሳኤ ግጥሞች
Skip Navigation Links
ቤተልሔም እንሂድ ሉቃ ፪፥፲፭
የ፲ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ፎቶ
ኪነ-ጥበብ
የግብጽ በረሐ ራብ ውኃ ጥሙ፣
የስጋቱ መንገድ መከራ ድካሙ፣
ገና ሳይታሰብ ገና ሳይጀመር፣
የድንግል ማርያም የስደትዋ ነገር፣
በሌሊት ሊናገር የሽሽትዋን ጉዳይ፣
የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሳይታይ፣
ከአረጋዊው ስምዖን ድንግል ሰምታ ነበር፣
በነፍስሽ ጦር ያልፋል እያለ ሲናገር።
(ተጨማሪ ያንብቡ )

በገሊላ ቃና በዶኪማስ ቤት
ድንግል አዛኝቱ የአምላክ እናት
እድምተኛው  በዝቶ ወይኑ ሲያልቅባቸው
ጥብብ ጭንቅ ሲሉ ማጠፍያው አጥሯቸው
ወይኑ በማለቁ ዳር ይደርሳል ያለው
ተክዟል ዶኪማስ አለሁልህ በለው
ልጄ ወይኑ አለቀ ብለሽ ስትነግሪው
ጌታም በመታዘዝ ልዩ ወይን ሰጣቸው
ብለሽ እንዳማለድሽ ከእፍረት እንዳዳንሽው
ስለእኔም ባዶነት የኔ ጌታ በይው:: (ተጨማሪ ያንብቡ )

   
ጠቃሚ ድረ-ገጾች
Skip Navigation Links
  ያለፉ ጽሁፎች..፩  |