፲፩ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በዴንቨር ኮሎራዶ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ ፳፱, ፳፻፫ ዓ.ም (Sep. 02, 2011)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ፲፩ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በዴንቨር ኮሎራዶ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ ፳፱, ፳፻፫ ዓ.ም (Sep. 02, 2011) ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣጤዎስ የሰሜን ምእራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ካህናት ተጋባዥ መምህራን እንዲሁም ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ የጉባኤው ተሳታፊዎች በተገኙበት ጉባኤው ከምሽቱ 12:00 (6:00 PM) በጸሎት ተጀመረ በማስከተልም የፈለገ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ተወካይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣጤዎስም <<አስተጋብኦሙ ለሀውርት እምጽባህ"="">> ከሚለው ከቅዱስ ያሬድ ድርሰት በተወሰደ ኃይል ቃል መሰረት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከወጣቱ ትውልድ የምትጠብቀውን መጠነ ሰፊ አገልግሎት በዝርዝር አውስተው በተጨማሪም የጉባኤው ተሳታፊዎች በመጪው ቀናት የሚካሄዱትን መርሃ ግብሮች በንቃት እንዲሳተፉ በማሳሰብ የእለቱን ትምህርታቸውን አጠናቀዎል:: በማጠቃለያም የሰ/ት/አ/ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ብዙአየሁ ልመንህ በቀጣዮቹ ቀናት የሚካሄዱትን መርሃ ግብሮች በዝርዝር በመግለፅ እና ጉባኤውን ለመሳተፍ ለመጡት ተሳታፊዎች የሚጠበቅባቸውን የተሳታፊነት ድርሻ የሚገልጽ መልእክት አስተላልፈዋል:: በማጠቃለያም የእራት መስተንግዶ ከተደረገ በኃላ የእለቱ መርሃ ግብር ከምሽቱ 3:00 (9:00 PM ) ተፈፅሟል::
|
|