በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
መዝሙርና ምሥጢራዊ ሥርዓቱ
መዝሙር ወይም ዜማ የተጀመረው በአራቱ ሰማያት ማለትም በሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ በኢዮር፣ በራማና በኤረር ያሉ መላእክት እግዚአብሔር ፈጣሪያቸውን ያለ ዕረፍት ሲያመሰግኑት ነው። ይህንንም ሲያረጋግጥ ነቢዩ ኢሳይያስ፦ “እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ሊይ ተቀምጦ አየሁት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሰማይና ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር። የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ። ቤቱንም ጢስ ሞላበት” ይላል (ኢሳ ፮፤ ፩-፭)። ይህም በመላእክት የተጀመረው ጣዕመ ዜማ በእነሱ አሰሚነት ለሰው ልጆችም ተላልፏል። ይህም ይታወቅ ዘንድ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሥልጣነ እግዚአብሔር እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አገዛዝ ነፃ ባወጣበት ጊዜ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ በደረቅ ምድር ቢያሻግራቸው ሙሴና ተከታዮቹ በተለይም እኅቱ ማርያም በከበሮ ድምጽ እየታጀቡ እግዚአብሔርን በጣዕመ ዝማሬ አመስግነዋል፤ የመዝሙርም በይፋ መጀመር የታወቀው በዚሁ ጊዜ ነው (ዘጸአ ፲፭፤፳፪)። ደግሞም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ባየው ራእይ ምዕ ፲፬፤፩-፮ በምድር የተዋጁት አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ወገኖች ማንም ያልዘመረውንና ሊዘምረው የማይችል ጣዕሙ ልዩ የሆነ አዲስ መዝሙር በመድኃኒታችን ዙፋን ፊት በኪሩቤልና ሱራፌል መካከል እንደዘመሩ ይገልጻል።( ተጨማሪ ያንብቡ
) |
|