ዕቅድ ክፍል በዚህ ክፍል ስር ሰንበት ት/ቤቶች ትላንትና እና ከትላንት ወዲያ የመጡትበትን መንገድ በመመርመር ለነገ የተሻለ እና የሰመረ አገልግሎት የሚበጀዉን መንገድ ቀድሞ መመልከት ነው። ሁሉም የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች የሚሳተፉበትንና የሚቀራረቡበትን ጎዳና መመንጠር የዚህ ክፍል የመጀመሪያ ተግባሩ ነው። በቆየ የአገልግሎት ጊዜያቸው አርቆ ማሰብና አጥርቶ ማየት የተቸሩ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በማስተባበር መንገዳችንን ቀድመው እንዲያዩልን በማድረግ ወደ ተሻለ የአገልግሎት ጥግ መድረስ ነው። በዛውስ ላይ ክርስቲያን ዛሬ ላይ ሆኖ ስለ “ነገ” የሚኖር የሁለት ዘመን ሰው ስለመሆኑ ለማን ምን ተብሎ ይነገራል ?
 Contact Information:

Contact person


Bereket Tesfaye
NASSU Planning Dept
EOTCNASSU.PLANNING@GMAIL.COM

615-554-1589