መካከለኛው አሜሪካ ሀገረ ስብከት
አንቀጽ 2፡- አከላለል  በሰሜን አሜሪካ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባዔ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5 መሠረት ይህ የአንድነት ጉባዔ ተጠሪነቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ይሆናል፡፡ የየክፍለ ግዛቶች ተጠሪነት ደግሞ በሀገረ ስብከቱ ሥር ላለው ለሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ ሥራ አስፈጻሚ ይሆናል፡፡  የየቅርንጫፎች አከላለል በሰሜን አሜሪካ በሁሉም አካባቢ ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት በ4 ቅርንጫፍ የከፈለ ነው፡፡ ወደፊት ግን የአንድነት ጉባኤው መዋቅር በተሞክሮ እየታየ ሲመጣና ሲጠናከር የአከላለሉ መሰረታዊ የሆኑ ነጥቦች ሊካተቱበትና እንደገና ሊታይ ይችላል፡፡